ኢራን በኳታርና በኢራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሟን የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
ኢራን በአሜሪካ ለተፈጸመባት ጥቃት የአጸፋ ምላሽ መስጠት መጀመሯን ነው መገናኛ ብዙሃኑ የገለጸው፡፡
በመንግሥት የሚተዳደረው የታስኒም የዜና ወኪል፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ የፈጸመው የሚሳኤል ጥቃት በኳታር እና በኢራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ዘግቧል።
በኳታርም ፍንዳታዎች መሰማታቸውን በቅርብ የወጡ ሪፖርቶች ማመላከታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ይሁን እንጂ የኢራን ድርጊት በኳታር መንግስት ውግዘት ገጥሞታል፡፡
የኳታር መንግስት፣ በአል-ኡዴድ የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በጽኑ አውግዟል።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጅድ አል-አንሷሪ በኤክስ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “ይህ የኳታርን የግዛት ሉዓላዊነት፣ የአየር ክልሏን፣ የዓለም አቀፍ ህግን እና የተባበሩት መንግስታት ቻርተርን የሚጋፋ ከባድ ጥሰት አድርገን እንቆጥረዋለን” ብለዋል።
በታምራት ቢሻው