በመዲናዋ በተከፈቱ የገበያ ማእከላትና ባዛሮች በቂ ምርት እየገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ንግድ ቢሮ አስታወቀ

You are currently viewing በመዲናዋ በተከፈቱ የገበያ ማእከላትና ባዛሮች በቂ ምርት እየገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ንግድ ቢሮ አስታወቀ

AMN ጳጉሜ 5/13/2017

በመዲናዋ የተከፈቱ 20 ባዛሮችን ጨምሮ በ219 ቅዳሜና እሁድ ገበያ እና 5ቱም ገበያ ማዕከላት በቂ ምርት እየገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ንግድ ቢሮ አስታዉቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ቢሮው ከኦሮሚያ ክልል ጋር በፈጠረዉ የገበያ ትስስር ተጨማሪ የግብርና ምርቶች ወደ መዲናዋ እየገቡ ነዉ፡፡

ከዘመን መለወጫና ሌሎች በአላት በዓል ጋር በተያያዘ 219 የቅዳሜና እሁድ ገበያ ፤ አምስት የገበያ ማዕከላት እና 20 ባዛሮች በመዲናዋ መከፈታቸዉን ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ገልጸዋል፡፡

ከኦሮሚያ ክልል ጋር በተፈጠረዉ በዚህ የገበያ ትስስር የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ጨምሮ የእንስሳት ተዋፅኦዎችና ሌሎች የበአል ምርቶች በቂ ሁኔታ እየገቡ መሆናቸዉን የአዲስ አአባ ከተማ አስተዳድር ንግድ ቢሮ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review