ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሃላባ እና ከምባታ ዞኖች በክረምት በጎፈቃድ መርሃግብር የተገነቡ ሞዴል የገጠር መንደሮችን ማስረከባቸዉን ገለጹ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሃላባ እና ከምባታ ዞኖች በክረምት በጎፈቃድ መርሃግብር የተገነቡ ሞዴል የገጠር መንደሮችን ማስረከባቸዉን ገለጹ

AMN መስከረም 28/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ በክረምት በጎፈቃድ መርሃግብር በሃላባ እና ከምባታ ዞኖች የተገነቡ ሞዴል የገጠር መንደሮችን አስረክበናል ብለዋል፡፡

እነኚህ መንደሮች የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮችን ሕይወት ለማሻሻል የምናደርገው ጥረት ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ናቸው። ቤቶቹ የፀሃይ ኃይል ማመንጫ የተገጠመላቸው፣ ለማብሰል ደግሞ ከእንስሳት እዳሪ ባዮጋዝ የሚጠቀሙ፣ የተለየ ሳሎን፣ መጸዳጃ እና ሰርቪስ ቤቶች የተሟላላቸው ናቸው።

ንጽህናን በሚያረጋግጥ እና የአኗኗር ደረጃን ከፍ በሚያደርግ አኳኋን የተለየ የእንስሳት በረት ተሰርቶላቸዋል። እነዚህ የገጠር ኮሪደር ልማት መንደሮች የገጠሩን አኗኗር የማሳደግ ሕልማችን አካል በመሆን ተስፋፍተው የሚሰሩ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ሰባት አመታት የክረምት በጎ ፈቃድ በከተሞች ለሚኖሩ ለችግር የተጋለጡ ወገኖች መኖሪያ ቤቶችን ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ በገጠር ኮሪደር ልማት የሥራውን እመርታ ወደገጠር አስፋፍተናል። ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና የዲያስፖራው ማኅበረሰብ እነኚህን ሥራዎች እንዲደግፉ እና እንዲሳተፉ አበረታታለሁ።

ባለፈው ጉብኝቴ ወቅት ያቀረብኩላቸውን የቤትሥራ በመወጣት በአጭር ጊዜ ውስጥ በራስ አቅም የሀምበሪቾ ተራራ ደረጃንም በእጥፍ ሠርተው ላጠናቀቁት አመራሮች ያለኝን ምስጋና አቀርባለሁ። ወደፊትም የየአካባቢ አመራሮች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሠሩትን ሞዴል መንደሮች በመጪው አመት በየዞኑ ወደ100 ቤቶች እንዲያሳድጉ አሳስባለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review