የኤ ኤም ኤን እንግሊዘኛ ክፍል ባልደረባ ጋዜጠኛ አፈወርቅ ውበቱ በአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት በAfrican life style ዘርፍ ከመጨረሻወቹ ሶስት እጩወች አንዱ ሆነ

You are currently viewing የኤ ኤም ኤን እንግሊዘኛ ክፍል ባልደረባ ጋዜጠኛ አፈወርቅ ውበቱ በአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት በAfrican life style ዘርፍ ከመጨረሻወቹ ሶስት እጩወች አንዱ ሆነ

AMN-ሕዳር 25/2018 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ለአፍሪካ ሚዲያ አዋርድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።

ከስካይላይት ሆቴል እየተካሄደ የሚገኘውን የሽልማት መርሀግብር ሙሉ የቀረጻ መሳርያ እና ባለሙያወችን ከመርሀግብሩ አዘጋጅ ጋር በመቀናጀት እያከናወነ ይገኛል።

የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች መርሀግብሩን እየታደሙ ሲሆን የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የእንግሊዘኛ ክፍል ባልደረባ ጋዜጠኛ አፈወርቅ ውበቱ በ African life style ዘርፍ ከመጨረሻወቹ ሶስት እጩወች ውስጥ ገብቷል።

የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት የአፍሪካን የሚዲያ ገጽታ የሚቀርፁ ምርጥ ድምጾችን በማሰባሰብ ጋዜጠኝነትን፣ ብሮድካስትን፣ ዲጂታል ሚዲያን እውቅና የሚሰጥ ሽልማት ነው።

በቴሌቪዥን እና በኦንላይን መድረኮች የተለያዩ ምድቦች ያሉት፣ ከአህጉሪቱ የተውጣጡ የኢንዱስትሪውን መሪዎች ያካተተ የተከበረ የዳኞች ቡድን በአፍሪካ ሚዲያ የላቀ የልህቀት፣ የብዝሃነት እና የፈጠራ አገላለጽ መለኪያን አስቀምጧል።

የሚዲያ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ የተጋበዙ ሲሆን በየዘርፉ ያሉት ምርጥ ሶስት እጩዎች በአዲስ አበባ በሚደረገው የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።

እጩዎች በሙሉ የ2,000 ዶላር የገንዘብ ሽልማት የሚያገኙ ሲሆን የእያንዳንዱ ምድብ አሸናፊ በአጠቃላይ 6,000 ዶላር ሽልማት የሚበረከትላቸው ይሆናል።

መርሀግብሩ በስካሁን ምእራፍ በአራት ዘርፎች ያሸነፉ የሚዲያ ባለሙያወች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ቤተልሔም አየነው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review