AMN- ግንቦት 4 /2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያን ተሞክሮ ማካፈላቸውን አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላፉት መልዕክት ፣ በፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ አዘጋጅነት በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍያለሁ ብለዋል።

በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው ውይይት መድረክ ላይ ከተሞክሯችን የተቀዱ ከፍ ያሉ ሀሳቦች ተነስተዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በተነሱት ሁለት ዘርፎች የጀመረችውን ስራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን እንደምትቀጥልም አስፍረዋል።