የለማች፣ የተከበረችና የታፈረች ኢትዮጵያን እናፅና በማለት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ጥሪ አቀረቡ

You are currently viewing የለማች፣ የተከበረችና የታፈረች ኢትዮጵያን እናፅና በማለት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ጥሪ አቀረቡ

AMN – ሕዳር 29/2018 ዓ.ም

ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በፍትሕ እና በዕኩልነት መሠረቶች ላይ በማዋቀር የለማች፣ የተከበረችና የታፈረች ኢትዮጵያን ማጽናት ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገልጸዋል።

20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ዛሬ ተከብሯል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ ለ20ኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን በፍትሕና በእኩልነት መሠረቶች ላይ በማዋቀር የለማች፣ የተከበረችና የታፈረች ኢትዮጵያን እናፅና ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review