ከ8 ሺህ በላይ የእርባታ ዶሮዎች ለነዋሪዎች ድጋፍ ተደረገ

You are currently viewing ከ8 ሺህ በላይ የእርባታ ዶሮዎች ለነዋሪዎች ድጋፍ ተደረገ

‎AMN – ታሕሳስ 02/2018 ዓ.ም

‎የአራዳ ክፍለ ከተማ 8ሺህ 2መቶ ዶሮዎችን የስራ ተነሳሽነት እና ፍላጎት ላላቸው 5 መቶ 11 ለሚሆኑ ቤተሰቦች የእርባታ ዶሮዎችን ድጋፍ አደረገ ፡፡

‎ከክፍለ ከተማው ከ8ቱም ወረዳዎች ለተመለመሉ ነዋሪዎች የተሰጠው ይህ ድጋፍ ለሁለተኛ ዙር የተደረገ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ዙር 4 መቶ 30 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ መደረጉንም የአራዳ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደርቤ ተሾመ ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል።

‎ተጠቃሚዎች ከዚህ በፊት በራሳቸው ተነሳሽነት ዶሮዎችን እያረቡ የነበረ ሲሆን ይህንኑ መነሻ በማድረግ ስራቸውን እንዲያስፋፉና ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማረጋገጥ ክፍለ ከተማው በበጎ ፍቃድ ድጋፍ እንዳደረገላቸው በመርሃግብር ላይ ተነስቷል።

‎ድጋፉ በቤተሰብ ደረጃ የተደረገ ሲሆን ይህም የአንድ ቤተሰብ አባላት በአንድ ላይ በመደራጀት ሸማች ብቻ ሳይሆን አምራችም በመሆን ከራስ ፍጆታ አልፎ ለገበያ ምርት በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

‎በሔዋን አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review