4ኛው ዙር የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በተገኙበት ተጀምሯል፡፡
ክትባቱ ዕድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የሚሰጥ ሲሆን በዛሬዉ ዕለትም በየረር ጤና ጣቢያ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በዘመቻው በአዲስ አበባ ከ700 ሺህ በላይ ለሆኑ ህፃናት እንደሚሰጥ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ አስታዉቀዋል። ዛሬ የጀመረው ክትባቱን የመስጠት ዘመቻ ለተከታታይ አራት ቀናት በትምህርት ቤት ፣ ቤት ለቤት ፣ በህፃናት ማቆያ እና ማሳደጊያ ማዕከላት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
መከተብ የህፃናት መብት ማስከተብ ደግሞ የወላጆች እና አሳዳጊዎች ግዴታ መሆኑን የገለፁት ኃላፊዉ ከአንድ ወር በኋላም ሁለተኛ ዙር ክትባት እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
በትባረክ ኢሳያስ