አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘመናዊ ቴክኖሎጅን ከብቁ የሰዉ ኃይል ጋር በማቀናጀት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን ነቅሶ የሚያወጣና የአዲስ አበባ ከተማን ገጽታም ለዓለም የሚያጎላ መሆኑን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ተናገሩ፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና የአዲስ አበባ ከተማ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ዋርካን እና መሰል በጋራ የሚሠሯቸዉን ሥራዎች ለማጠናከር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ የአዲስሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጅን የታጠቀና በብቁ የሰዉ ኃይል የሚዘወር ተቋም መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሚዲያዉ የይዘት ማሻሻያ ከማድረግ ጀምሮ በሌሎች ዘርፎችም በሠራቸዉ ሥራዎች አሁን ላይ የአዲስ አበባ የመጀመሪያ የመረጃ ምንጭ እና ትዉልድ ተሻጋሪ የመረጃ ቋት በመሆን ተመራጭነት እና ተወዳዳሪነቱን በተግባር እያረጋገጠ ነዉ ብለዋል፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እና የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በቅንጅት በመሥራት እዉነተኛ መረጃን መጋቢ መንግስት አና ሕዝብም የጋራ ተግባቦት ይኖራቸዉ ዘንድ በጋራ የሚሠሩትን ሥራ አጠናክረዉ ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
ለሚዲያዉ ስኬታማ ጉዞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚደርገው ድጋፍ ሚናዉ የጎላ ነዉ ያሉት አቶ ካሳሁን በቀጣይም ሚዲያዉ የሕዝብና የመንግስት የመረጃ ፍሰት መደላድልነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በተመስገን ይመር