ሪሞታችሁን ወደ ሌላ ቴሌቪዥን የማያስቀይር ለሁሉም ቅርብ እና አጓጊ የሆነ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሊቀርብ ነው፡፡
ውብ አዲስ ድራማን ለአለፉት ሀያ አመታት አፍኜ ይዤው የነበረ ድርሰት ነው። ይዤ ያቆየሁት የሚመጥነው አቅም እና ሚዲያ እስኪያገኝ ነበር ሲል የውብ አዲስ ድራማ ደራሲ እና ዳይሬክተር አቶ ቴድሮስ ተሾመ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል፡፡
ውብ አዲስ ድራማ በይፋ የተበሰረበት መድረክ ላይ የድራማው ደራሲ እና ዳይሬክተር አቶ ቴድሮስ ተሾመ እንደተናገሩት ይህ ጊዜ አዲስ አበባ እኳን ለጎብኝዎች ለኗሪዎቿ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ እየተለወጠች ነው ብለዋል።
ይህንን ለውጥ ተከትሎ እንዲህ አይነት ድራማ ለተመልካች ማቅረብ መቻል በታደል ነው ሲሉ ይገልጿል፡፡
ድራማው ልብ ሰቃይ በሚባል ደረጃ የተዘጋጀ እንዲሁም ከዘጠና ከመቶ ከቤት ውጭ የሚቀረጽ፣ በድርጊት የተሞላ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ነው ብለዋል።

በአብዛኛው አዲስ አበባ ላይ የሚቀረጽ ሲሆን ሞሮኮ እና ጋና ላይም እንደሚቀረጽ አቶ ቴወድሮስ ገልፀዉ፤ በተጨማሪም የሞሮኮ እና የጋና ተዋንያችም በትወና እንደሚሳተፉ አስረድተዋል፡፡
ተከታታይ ፊልሙ ልብ ሰቃይ ከመሆኑም ባሻጋር የፖሊስ ክትትል፣ የሚያጓጓ የፍቅር ታሪክ፣ አስተማሪ የሆነ የቤተሰብ ታሪክ ያለው እጅግ አጓጊ አንጋፋ እና ታዋቂ የሀገራችን ተዋናዮች የሚሰሩበት ተከታታይ ድራማ ነው፡፡
ውብ አዲስ ድራማ አዳዲስ መሪ ተዋናዮችን በህዝብ ፊት መመልመሉ ልዩ ያደረግዋል ሲል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ይህም መሪ ተዋናዮች ሀምሳ ከመቶ በህዝብ ድምጽ እና ሀምሳ ከመቶ በዳኞች ወሳኔ እንደሚመረጡ አብራርተዋል፡፡
በፍሬሕይወት ብርሃኑ