የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “የምሁራን ሚና ለሀገራዊ ብልጽግና” በሚል ርዕስ የጥናታዊ ጽሁፍ እያቀረቡ ይገኛሉ።

የአካዳሚያዊ አመራሮችና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ገለጻው እየተሰጠ ይገኛል። የዛሬው መርሃ ግብር 75ኛ ዓመት በዓሉን ለማክበር ላለፉት ሳምንታት ሲደረጉ የነበሩ ተከታታይ ገለጻዎች እና ፕሮግራሞች ማጠቃለያ ነው። – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት