አዲስ አበባን በአፍሪካ ለሕፃናት ማሳደግ ምቹና ተመራጭ ከተማ ለማድረግ የተጀመረዉ ሥራ ፍሬ እያፈራ እንደሚገኝ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing አዲስ አበባን በአፍሪካ ለሕፃናት ማሳደግ ምቹና ተመራጭ ከተማ ለማድረግ የተጀመረዉ ሥራ ፍሬ እያፈራ እንደሚገኝ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN ታኅሣሥ 24/2018

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት አዲስ አበባን በአፍሪካ ለሕፃናት ማሳደግ ምቹና ተመራጭ ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ሥራ ፍሬ እያፈራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በከተማችን እየተተገበረ ባለው የቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሃ ግብር አማካኝነት፣ በየሰፈሩ የለየናቸው ውስብስብ እና ከፍተኛ የአካል ጉዳት ያለባቸው 177 ሕፃናት እንደየጉዳታቸው ሁኔታ የተዘጋጁ ምቹ ዊልቸሮች ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ብለዋል፡፡

ዊልቸሮቹ እንደየሕፃናቱ የአካል ጉዳት ሁኔታ ተስማሚ ሆነው መሠራታቸው ለሕፃናቱ ምቹና ውጤታማ ድጋፍ እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል። ይህም የአካታችና ሁሉን አቀፍ ልማታችን አካል ሲሆን፣ ከተማችን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ትሆን ዘንድ በቀጣይ ተደራሽ ያልሆኑ ሕፃናትን ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንሰራለን።

ይህንን በጎ ተግባር ያስተባበራችሁና አብራችሁን በቅርበት እየሠራችሁ ያላችሁ አጋሮቻችንን፣ በተለይም የክሊንተን ሄልዝ አክሰስ ኢኒሼቲቭን በተጠቃሚ ሕፃናትና ወላጆቻቸው ስም ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review