የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ሴራ” በዓልን ምክንያት በማድረግ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው

You are currently viewing የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ሴራ” በዓልን ምክንያት በማድረግ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው

AMN AMN- ጥር 02/2018 ዓ.ም

የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የሆነውን ሴራ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በሲምፖዚየሙ ላይ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የሀላባ ዞን እና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ዲያስፖራዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ናቸው፡፡

በዚሁ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የሀላባ ዞን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ መሀመድ አሚን መሃዲ የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ሴራ በዓል ሁለት ትላልቅ ክዋኔዎችን የያዘ መሆኑን ጠቁመው የመጀመሪያዉ ከአሮጌ ዘመን ወደ አዲስ ዓመት ሽግግር የሚደረግበት እና ሁለተኛው ደግሞ ከልጅነት ወደ አዋቂነት የእድሜ ሽግግር የሚደረግበት መሆኑን ገልጸዋል።

የሀላባ ሴራ ብሄረሰቡ የሚተዳደርበት ባህለዊ ህግ ወይም ደንብ ማለት እንደሆነ ያወሱት ኃላፊው ከ13ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ አልፎ ዛሬ ላይ የደረሰ ነው ብለዋል፡፡

በአሁን ሰዓት እያንዳንዱ ብሄር እራሱን በራሱ የማልማት ባህሉን፣ ታሪኩን፣ ቋንቋዉንና የአስተዳደር ስርዓቱን እንዲመራ በተፈጠረው እድል ብሔረሰቡ በአዳባበይ ባህሉንና እሴቱን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም አፈ ጉባኤው ገልጸዋል።

የሀላባ ሴራ መደገጋፍን፣ አብሮነትንና አንድነትን የሚያበረታታ፣ በህዝቦች መካከል ሰላም በማስፋን ማህበረሰቡ ሀይማኖት፣ ብሄር፣ ዘር፣ ቀለም ሳይለይ አብሮ የማኖር እሴት የሚያጠናክር መሆኑም ተገልጿል።

በዓሉን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ተብሏል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review