ወንዞችን ከብክለት በማፅዳት ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትን እንዲያጎናጽፉ ማድረግ ተችሏል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ “በአዲስ አበባ ወንዞች ትንሣኤ” ዘጋቢ ፊልም በመዲናዋ የተከናወኑ የወንዝ ዳርቻና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ተዘዋዉረዉ በመጎብኘት ገለጻ አድርገዋል።
ወንዞች ለከተማ መቆርቆር፣ ለከተማ ውበት፣ ለከተማ ልማት ዋና መሰረት መሆናቸዉን ያነሱት ከንቲባዋ የመዲናዋ ወንዞች ግን አካባቢን በመበከል የጤና ጠንቅ ሆነዉ መቆየታቸዉን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ወንዞች የወንጀለኞች መደበቂያ በመሆን ጭምር ህብረተሰቡን ለተለያዩ ጉዳቶች ዳርገዋል።
ወንዞቹ ከየመጸዳጃ ቤቱ በሚወጣው ፍሳሽ ተበክለው
ማንነታቸውን አጥተው ጥቅም አልባም ሆነው ቆይተዋል።
አጠቃላይ ስለ አዲስ አበባ ወንዞች ልማት በተደረገው ጥናት አዲስ አበባ ላይ የሚገኙ 76 ወንዞች በቀጥታ ከመጸዳጃ ቤት በሚወጡ ፍሳሾች የተበከሉ መሆናቸውን ጥናቱ አመላክቷል ብለዋል።
ከለውጡ አስቀድሞ በነበሩ ጊዜአት በዘርፉ በቂ ልምድና እውቀት አለመኖሩ ለችግሩ መባባስ በር ከፋች መሆኑን ጠቁመዋል።
በለውጡ ማግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ወንዞቻችንን እናጽዳ : ሸገርን እናስውብ በሚል መርህ እና አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናድርግ በሚለው ትልቅ ራዕይ ወንዞችን የማልማት ሥራዉ ስራው መጀመሩን አንስተዋል።
በሚካኤል ሂሩይ