የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን አስመረቀ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን አስመረቀ

AMN-ጥር 07/2018

የሰላም ሰራዊት አባላት በአዲስ አበባ የተጅመረወን የማያቋርጥ ልማትና ለውጥ የተሳለጠ እንዲሆን ከሕዝብ እና ከመደበኛ ጸጥታ ኃይል ጋር በመቀናጀት እየሰሩ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በንድፈ ሃሳብና በወታደራዊ መስክ ያሰለጠናቸውን 22 ሺ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አስመርቋል።

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በምርቃው ወቅት እንደተናገሩት የሰላም ሰራዊት አባላት በአዲስ አበባ የተጅመረወን የማያቋርጥ ልማትና ለውጥ የተሳለጠ እንዲሆን ከሕዝብ እና ከመደበኛ ጸጥታ ኃይል በመቀናጀት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከመደበኛ ጸጥታ ኃይል ጋር በመቀናጀት የዛሬ ተመራቂዎችን ጨምሮ ከ 200 መቶ ሺህ በላይ የሰላም ሰራዊት አባላት ፣ ከ ዘጠኝ ሺህ በላይ የሕዝብ ቅጥር ጥበቃዎች ፣ ከ 40 ሺህ በላይ የግል ጥበቃ ኤጀንሲ ጥበቃዎች የከተማዋ ሰላም ለማጽናት በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ባለፉት አመታት ሐይማኖታዊ ፣ ባህላዊ ፣ የአደባባይ በዓላት እና ልዩ ልዩ ኩነቶች ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ የሰላም ሰራዊት አባላት ሁነኛ የጸጥታ ኃይል አጋዥ ናቸው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ ለወንጅል መንስኤ የሆኑት ምክኒያቶችን ቀድሞ በመለየት በወንጀል ለመቀነስ በርካታ ተግባራት መስራት ተችሏል ብለዋል።

በዚህም በሕዝብ እና በጸጥታ ኃይል ቅንጅት በተስራ ተግባራት ከተማዋ በአስተማማኝ ሁኔታ ዓለም አቀፍ አና ሀገር አቀፍ ኮንፈረንሶችን ማስተናገድ ችላለች ብለዋል ኮሚሽነሩ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራን ጨምሮ የከተማ እና የክፍለ ከተማ አመራሮች በምረቃ መርሃግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review