ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክርስቲያኖች ዘንድ ጥምቀት የመገለጥና የእርቅና ዳግም የመወለድ ምልክት መሆኑን ገልጸዋል።
በሀገራችን ካሉት ደማቅ የአደባባይ በዓላት አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል ድንቅ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶች ጎልተዉ የሚታዪበት ከመሆኑ ባሻገር፥ በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ፥ በርካታ የውጭ ሃገር ቱሪስቶች የሚታደሙበት፥ የሃገራችንን መልካም ገጽታ ለዓለም የሚያስተዋዉቅ ደማቅ በዓል ነው ብለዋል።
ይህንን ዉብና ደማቅ በዓል ከሃይማኖታዊ ልዩ ሥርዓቶቹ በተጨማሪ ባሕላችንን፣ ቋንቋችንን ዜማችንን፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በዐደባባይ የምናሳይበት በመሆኑ በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት ባሕል ሃይማኖታዊ ስርዓቱንና እሴቶቹን ጠብቆ በማክበር የበለጠ ሀገራችንን ለአለም እናስተውዋቅበታለን ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።