በኮሎምቢያ እና ቬንዙዌላ ድንበር አቅራቢያ በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ የፓርላማ አባልን ጨምሮ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ

You are currently viewing በኮሎምቢያ እና ቬንዙዌላ ድንበር አቅራቢያ በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ የፓርላማ አባልን ጨምሮ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ

AMN- ጥር 21/2018 ዓ.ም

በኮሎምቢያ ምስራቃዊ የቬንዙዌላ ድንበር አቅራቢያ 15 መንገደኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች አውሮፕላን ተከስክሳ የሁሉም ተጓዦች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

ከሟቾች መካከል ሁለት የበረራ ሰራተኞች፣ አንድ የኮሎምቢያ የፓርላማ ተወካይ እና በመጪው ምርጫ የሚወዳደሩ አንድ እጩ አባል ይገኙበታል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ “ሀገሪቱ በከባድ ሀዘን ላይ ትገኛለች” ብሏል።

አውሮፕላኑ የጠፋው ጥቅጥቅ ባለ ደን እና አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ባለበት አካባቢ በመሆኑ የፍለጋ ስራው ፈታኝ እንደነበርም ተገልጿል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ማሪያ ፈርናንዳ ሮጃስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተው፣ ስለ አደጋው መንስኤ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በመንግስት በሚተዳደረው ‘ሳቴና’ አየር መንገድ የምትመራው ይህች አውሮፕላን፣ ከኩኩታ ወደ ኦካኛ በመጓዝ ላይ እያለች ነው ከራዳር እይታ ውጭ የሆነችው።

የአካባቢው የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እንደገለጹት፣ አውሮፕላኑ ኦካኛ ለመድረስ 11 ደቂቃዎች ሲቀሩት ድንገተኛ የከፍታ መቀነስ አሳይቷል።

የሲቪል ኤሮኖቲክስ አስተዳደር የአደጋ ምርመራ ዳይሬክቶሬት “HK4709” ከተሰኘችው ከዚሁ አውሮፕላን ጋር ግንኙነት የተቋረጠበትን ምክንያት መረጃ በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review