AMN – ጥር 22/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ የስንዴ ፕሮግራም ምርታማነትን በመጨመር፣ የመስኖ ሥርዓትን በማስፋት፣ የዘር አቅርቦት ሥርዓትን በማጠናከር ብሎም በዋና ዋና አካባቢዎች አነስተኛ አርሶ አደሮችን በመደገፍ የሀገራችንን ራስን የመቻል ጉዞ ግብ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ተርስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በ2018 የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሩብ ዓመታት አጠቃላይ የስንዴ ምርት 126.69 ሚሊዮን ኩንታል ደርሷል ብለዋል።
ይኽም የመስኖ ስንዴ ምርትን ሳይጨምር መሆኑን አመላክተዋል።
አርሶ አደሮቻችንን ማድነቅ እና ማመስገን እፈልጋለሁ ያሉት ጠቅላ ሚኒስትሩ፣ “ይህንን የሥራ ጽናት ቀጥሉበት” ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡