ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን በማሸነፍ ለፍፃሜ ደረሰ

You are currently viewing ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን በማሸነፍ ለፍፃሜ ደረሰ

AMN ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም

በካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን 3ለ1 አሸንፏል።

በኢትሃድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ግብፃዊው አጥቂ ኦማር ማርሙሽ ሁለት ግቦችን በስሙ አስመዝግቧል። አማካዩ ቲጃኒ ራይንደርስ ሌላኛውን ግብ አስቆጥሯል።

የኒውካስትልን ብቸኛ ግብ አንቶኒ ኢላንጋ ማስቆጠር ችሏል።

የመጀመሪያውንም ጨዋታ 2ለ0 አሸንፎ የነበረው ማንችስተር ሲቲ በድምር ውጤት 5ለ1 በማሸነፍ ለፍፃሜ ደርሷል።

ሲቲ በፍፃሜው አርሰናልን በዌምብሌይ የሚገጥም ይሆናል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review