ኢትዮጵያ ታምርት የሉዓላዊነታችን መሠረት፣ የብልጽግናችን ምሦሶ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ታምርት የሉዓላዊነታችን መሠረት፣ የብልጽግናችን ምሦሶ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN — ሚያዚያ 30 / 2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ታምርት የሉዓላዊነታችን መሠረት፣ የብልጽግናችን ምሦሶ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ዘርፍ እያሳየችው ያለው ተጨባጭ ዕድገት የብልጽግናችን ማብሠሪያ እየሆነ ይገኛል ብለዋል።

ዛሬ በአራተኛው የ”ኢትዮጵያ ታምርት” ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ማጠቃለያ ላይ የተመለከትናቸው የጥራትና የፈጠራ ውጤቶች የሀገራችንን የማምረት ዐቅም በተግባር የሚያረጋግጡ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዓት የሚረጋገጠው በምርት ራስን በመቻል መሆኑን በመገንዘብ የተጀመረው ይህ ንቅናቄ ተኪ ምርትን በማሳደግ፣ የፋብሪካዎችን ዐቅም በመገንባት እና የሥራ ባህልን በመለወጥ ረገድ ከፍተኛ ስኬት አስመዝግቧል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

አምራች ኢንዱስትሪው የኢኮኖሚያችን የልብ ትርታ ሆኖ እንዲቀጥል ሦስት መሠረታዊ ጉዳዮች ወሳኝ ናቸው ያሉ ሲሆን እነሱም፦ ታሪክን መቀየር የሚችል ኢንዱስትሪያዊ አመለካከት፣ አቋራጭ ትርፍን የሚጸየፍ ታታሪ ባለሀብት እና በየፋብሪካው እየተገኘ ችግር የሚፈታ እጀ ንጹሕ አመራር ናቸው ብለዋል።

መንግሥት ለዘርፉ ምቹ ፖሊሲዎችንና ድጋፎችን ማመቻቸቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ቀጣዩን ኤክስፖ ይበልጥ በፈጠራና በስብጥር የላቀ ለማድረግ ከአሁኑ በትጋት እንሠራለን ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review