AMN ጥር 29/2028 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰፊ፥ ንጹሕና ምቹ የተሽከርካሪ፣ የብስክሌትና የእግረኛ መንገዶችን በመገንባት ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መንገዶች እንዲኖራት ማድረግ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የስድስት ወራት ሪፖርት ለምክር ቤቱ ባቀረበቡት ወቅት 17 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የመንገድ ሽፋን፣ የትራፊክ ፍሰት፥ የመንገድ ደኅንነት የማሻሻል የግንባታ እና የጥገና ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

ከንቲባዋ በሪፖርታቸው እንደገለጹት ከ134 ኪ.ሜ. በላይ አዲስ የመንገድ ግንባታ እና ከ573 ኪ.ሜ በላይ የመንገድ ጥገና በማካሔድ በድምሩ በግማሽ ዓመቱ ከ708 ኪ.ሜ በላይ ግንባታ ማከናወን ተችሏል።
በዚህ ግማሽ ዓመት አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መንገድ እንዲኖራት ማድረግ መቻሉ ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡
በትዝታ መንግስቱ