ጥር 30/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከታሪክ ባሻገር ታሪክ ገላጭ ስራዎች ያስፈልጋሉ ሲሉ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሎጎ ሐይቅ ሪዞርትን በይፋ መርቀዋል፡፡
የሎጎ ሐይቅ እና የ800 ዓመት ዕድሜ ያለዉ ገዳም በበርካቶች ሊጎበኝ የሚገባዉ ታላቅ ዓላማን የያዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሎጎ ሐይቅ የተገነባዉ ሎጅና የአካበቢዉ ታሪክ በሁሉም ጫፍ ትምህርት የሚወሰድበት እንዲሆን ከታሪኩ ባሻገር ታሪክ ገላጭ ሥራዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡
ከየትኛውም ጫፍ ጊዜውንና ገንዘቡን ሰውቶ ሐይቅ የመጣ ሰው፣ ቢያንስ ቢያንስ ታሪክ ሳይማር፣ ፍቅር ሳይጎነጭ፣ ደስታና ሰላምን ሳያጣጥም ወደመጣበት አይመለስም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ::
እኛ አካባቢዉን በጎበኘንበት ወቅት ያስተዋልነው ታሪክ እና የሰው ፍቅር መኖሩን ብቻ ሳይሆን አየሩ በራሱ ሰላም ያለው የማይጠገብ መሆኑን ነዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ከጎርጎራ በመቀጠል በአማራ ክልል የ’ገበታ’ ውጥን ሁለተኛው ፕሮጀክት ሲሆን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር በግብርና፣ በትራንስፖርት፣ በቱሪዝምና በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ መነቃቃትን የሚፈጥር ነዉ፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ