አዲሱ የስማርት ፖሊስ ጣቢያ አገልግሎት ለማኅበረሰቡ ምን ጥቅም ይሰጣል?

You are currently viewing አዲሱ የስማርት ፖሊስ ጣቢያ አገልግሎት ለማኅበረሰቡ ምን ጥቅም ይሰጣል?

👉 አገልግሎቱ የፖሊስን አገልግሎት ዲጂታላይዝ የማድረግ እና ማኅበረሰቡ በነጻነት ወይም ምንም አይነት ጫና ሳይደርስበት በቀላሉ የሚፈልገውን መረጃ ለፖሊስ ማድረስ ያስችለዋል።

👉 የወንጀል ጉዳይ፣ የተለያዩ አደጋዎች፣ የትራፊክ አደጋን ጨምሮ ማንኛውንም ጉዳይ በቀላሉ ለፖሊስ ማቅረብ የሚቻልበትን ስርዓት ነው።

👉 አገልግሎቱ ምንም አይነት የሰው ንክኪ ሳይኖር ተገልጋዩ በቀላሉ አገልግሎቱን ማግኘት ያስችላል።

👉 እስከዛሬ ስማርት ፖሊስ ጣቢያ አገልግሎት ላይ የዋለው በአውሮፓ እና እስያ ሶስት ሀገራት ሲሆን ዛሬ የተመረቀው በዓለማችን አራተኛው ስማርት ፖሊስ ጣቢያ በአፍሪካ ደግሞ የመጀመሪያው ያደርገዋል።

👉 ስማርት ፖሊስ ጣቢያው በፖሊስ ሥራ ላይ ቀልጣፋነትን (efficiency) በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል።

👉 ማንኛውም ባለጉዳይ ለፖሊስ ሪፖርት ካደረገ በኋላ ጉዳዩን ለመከታተል ያየው የነበረውን ውጣውረድ እና የማይመቹ ነገሮች ከሰው ጋር ያለውን ንክኪ እና ምልልስ በማስቀረት ጊዜና ጉልበት ይቆጥባል።

👉 በቴክኖሎጂው አማካይነት አመራሩ በቀላሉ መረጃ ስለሚደርሰው ቶሎ ውሳኔ አስተላልፎ የሚፈለግ ወንጀለኛ፣ የጠፋ ነገር ወይም የደረሰ ጉዳት ካለ ፖሊስ ቶሎ ደርሶ ያንን ችግር በፍጥነት መፍታት የሚችልበትን ዕድል ይፈጥራል።

👉 የወንጀል መከላከል እና የወንጀል ምርመራን ሥራን በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል።

👉 ፖሊስ በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ዕምነት እንዲያገኝ ያደርጋል።

👉 የሕግ አስከባሪው አካል የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አካል በመሆን ለማኅበረሰቡ መረጃን በቀላሉ በራሱ ስልክ ወይም በስማርት ጣቢያዎች አማራጭ እንዲይቀርብ ዕድል ይፈጥርለታል።

👉 ማኅበረሰቡ እያንዳንዱ ጉዳይ የፋይል ቁጥር ስለሚያገኝ በፋይል ቁጥሩ ጉዳዩን መከታተልና ፖሊስ ጣቢያ መሔድ ሳይጠበቅበት ተጨማሪ መረጃ ካለበት ቦታ ሆኖ መላክና እስከፍርድ ቤት ድረስ ጉዳዩን መከታተል ይችላል።

👉 በተለይ ግለሰቦች የተለየ መረጃ ይዘው ወይም ጉዳያቸውን ለኃላፊ መናገር ሲፈልጉ በቀላሉ እዚህ መጥተው ኃላፊውን በቀጥታ (live) እያገኙ በቀላሉ ጉዳያቸውን ማስረዳት የሚችሉበትን ዕድል ጭምር የፈጠረ ትልቅ ብሥራት ነው።

በሚካኤል ኅሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review