በአዲስ አበባ በሕገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ላይ ጥብቅ እርምጃ ሊወሰድ ነው

You are currently viewing በአዲስ አበባ በሕገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ላይ ጥብቅ እርምጃ ሊወሰድ ነው

AMM – መጋቢት 5/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ መደበቅና ሕገ-ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ በሚፈጽሙ አካላት ላይ የሕግ ማስከበር እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አስታወቁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገበያ ማረጋጋት፣ ሕገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥርና የኢትዮጵያ-አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ግብረ ኃይል ከአዲስ አበባ ማደያ ባለቤቶች ጋር እየመከረ ነው::

በዚህ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለፁት በተለይ በወር አጋማሽ እና በወር ማብቂያ ላይ በነዳጅ ማደያዎች አካባቢ የሚታየው ከፍተኛ ሰልፍ በከተማዋ የትራፊክ ፍሰት ላይ ጫና እያሳደረ ይገኛል ብለዋል።

በነዳጅ ማደያዎች በኩል የሚታዩ የነዳጅ መደበቅ ድርጊቶች እና ሕገ-ወጥ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎች ለችግሩ ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ድርጊቱም ነዳጅ ለሕብረተሰቡ በፍትሃዊነት እና በወቅቱ እንዳይደርስ እንቅፋት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ጃንጥርራ አባይ፣ በቀጣይ የሕግ ማስከበር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

በመዲናዋ ካሉ ተሽከርካሪዎች መካከል 70 በመቶው ቤንዚን የሚጠቀሙ መሆናቸውንና ቀሪዎቹ 30 በመቶው ደግሞ ናፍጣ የሚጠቀሙ መሆናቸዉንም የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ 132 የነዳጅ ማደያዎች መኖራቸውም ተመላክቷል፡፡

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review