ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በኩል ወደ ህንድ መጓዛቸው ተገለጸ

You are currently viewing ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በኩል ወደ ህንድ መጓዛቸው ተገለጸ

AMN መጋቢት 14/2018 ዓ.ም

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በኢራን መካከል ያለው ፍጥጫ እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ሁለት የነዳጅ ጫኝ መርከቦች (ታንከሮች) በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኩል ወደ ህንድ መጓዛቸው ተገልጿል።

መርከቦቹ በህንድ ውስጥ ለምግብ ማብሰያነት የሚያገለግል ፈሳሽ ጋዝ የጫኑ መሆናቸው ተነግሯል።

መርከቦቹ “የህንድ መርከብ እና ሰራተኞች” የሚል መልዕክት በማስተላለፍ በሰላም ማለፋቸው ነው የተዘገበው።

በመካከለኛዉ ምስራቅ ከተከሰተው ጦርነት ወዲህ በባህረ ሰላጤው በኩል የሚደረግ የንግድ እንቅስቃሴ በ95% መቀነሱን መረጃዎች ያሳያሉ።

በመቶዎች የሚቆጠሩ መርከቦች በባህረ ሰላጤው ውስጥ እና ውጭ መልህቃቸውን ጥለው የቆሙ ሲሆን፣ ይህም ወደ እስያ እና አውሮፓ የሚላኩ የምግብ፣ የኃይል እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች አቅርቦት እንዲቋረጥ አድርጓል።

በሺዎች የሚቆጠሩ መርከበኞች ደግሞ በባህረ ሰላጤው ውስጥ ተዘግቶባቸው እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት የባህር ላይ ኤጀንሲን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review