አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ከተሞች የማውንቴን ባይክ የሳይክል ውድድርን በቀጥታ ስርጭት ሊያስተላልፍ ነው

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ከተሞች የማውንቴን ባይክ የሳይክል ውድድርን በቀጥታ ስርጭት ሊያስተላልፍ ነው

AMN ሚያዝያ 19/ 2018 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ሚያዝያ 24 እና 25 በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ከተሞች የማውንቴን ባይክ የሳይክል ውድድርን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን መስጠት የሚያስችለውን ስምምነት ፈፀመ፡፡

ስምምነቱን የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ዲባባ እና የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ም/ል ፕሬዝደንት አቶ ሰለሞን በቀለ ፈርመዋል።

አቶ ሰለሞን ዲባባ ኤ ኤም ኤን ውድድሩን በብቃት ማስተላለፍ የሚያስችለው የሰው ሀይል እና የቴክኖሎጂ አቅም እንደገነባ ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ም/ል ፕሬዝደንት አቶ ሰለሞን በቀለ በበኩላቸው ኤ ኤም ኤን በቀጥታ ስርጭት በገነባው የላቀ ብቃት እና ባለው ደረጃቸውን የጠበቁ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ምክንያት መመረጡን ተናግረዋል።

ሚዲያው ለስፖርቱ ትኩረት በመስጠት እየሰራ የሚገኘው ስራም ለመመረጡ ሌላው ምክንያት ስለመሆኑ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ቴዎድሮስ ደበላ ገልፀዋል።

ውድድሩ የብስክሌት መሰረተ ልማት በስፋት የተገነባባትን እና በከፍተኛ የልማት ጎዳና ላይ የምትገኘውን አዲስ አበባን ለዓለም ማህበረሰብ በተሻለ ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ውድድር ላይ ከ35 የዓለም ሀገራት የሚመጡ ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ውድድሩም በ60 ሀገራት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል፡፡

በበላይነህ ይልማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review