አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ (መስከረም 17, 1933 – ሚያዝያ 11, 2001 ዓ.ም.)

You are currently viewing አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ (መስከረም 17, 1933 – ሚያዝያ 11, 2001 ዓ.ም.)

የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉሥ በመባል የሚታወቀው ታላቁ ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ ከ 20 ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ በተለየ ድምፁና ስሜት በሚጭሩ ዘፈኖቹ የሙዚቃ ኢንዱስትሪውን በመምራት በብዙዎች የሚወደድ የጥበብ ሰው ነው ።

የጥበብን ጉዞ ገና በልጅነቱ የጀመረ ሲሆን ከሃገር ፍቅር እስከ ዘበኛ ኦርኬስትራ፤ ከብሄራዊ ትያትር እስከ ካሴት ላይ ስራዎቹ አይረሴ ለመሆን ችሏል ፡፡

ጥላሁን በሙዚቃ ሙያው ከተሰለፈበት ጊዜ ጀምሮ ያልዳሰሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች አልነበሩም፡፡ ስለእናት፣ ስለሃገር፣ ስለፍቅር፣ ስለጀግንነት፣ ስለውበት… ያልዘፈነበት ርዕሰ ጉዳይ ፈልጎ ማግኘት ይከብዳል። የሙዚቃ ሰራዋቹ የነፍስ መነጋገሪያ ቋንቋ ሆነው ከዘመን ዘመን ተሻግረው እስካለንበት ጊዜ ዘልቀዋል፡፡

ጥላሁን ገሠሠ ብዙዎቹ ስራዎቹ የአማርኛ ዘፈኖች ሲሆኑ ከዛም ባለፈ የተወሰኑ የሙዚቃ ሰራዎቸ ደግሞ በአፋን ኦሮሞ እና በሱዳንኛ ዘፍኗል።

ለዘመናት የዘለቀ የሙዚቃ ስራው በአገር ውስጥና በውጭ አገር ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል።

ጥላሁን ለኢትዮጲያ ሙዚቃ ላደረገው አስተዋጽኦ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለማግኘት በቅቷል። በሌላ በኩል ህይወቱን በሙሉ ለሙዚቃ በማበርከቱ ከኢትዮጵያ ኪነጥበብና የብዙህን መገናኛ ሽልማት ድርጅት «የሙሉ ዘመን» ሽልማት ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል። ክብር ለዶክተር ጥላሁን ገሰሰ የዘመኑ ንጉሥ” በሚል ቅጽል ስምም በመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ክብር ተችሮታል ።

ጥላሁን ገሠሠ ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. በ68 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል ።

በብሩክታዊት ጥላሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review