የአዲስ አበባ የምገባ ማዕከላት እና ማህበራዊ ተደራሽነታቸው

You are currently viewing የአዲስ አበባ የምገባ ማዕከላት እና ማህበራዊ ተደራሽነታቸው

AMN- ግንቦት 10/ 2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት የምገባ ማዕከላት አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችንና የሀገር ባለውለታዎችን ለመደገፍ የተቋቋሙ ናቸው።

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በአጠቃላይ 29 የምገባ ማዕከላት ይገኛሉ።

ማዕከላቱ በዋናነት ትኩረት የሚያደርጉት ራሳቸውን መመገብ በማይችሉ እና እጅግ በጣም ተጋላጭ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ነው፡፡

ተጠቃሚዎቹም አረጋውያን፣ ቋሚ ገቢ የሌላቸው፣ አካል ጉዳተኞችን፣ የሀገር ባለውለታዎች እንዲሁም በየወረዳው ባሉ ማህበራዊ ኮሚቴዎች አማካኝነት የተመረጡ እጅግ ዝቅተኛ ኑሮ ያላቸው ነዋሪዎች ናቸው፡፡

እነዚህ የምገባ ማዕከላት በከተማ አስተዳደሩ እና በበጎ አድራጊ ባለሀብቶች ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፣ ዓላማቸውም በከተማዋ ውስጥ “ምንም አይነት የተራበ ሰው እንዳይኖር” ማድረግ ነው።

ማዕከላቱ በብዛት የተገነቡት አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በስፋት በሚኖሩባቸው እና ለትራንስፖርት ምቹ በሆኑ ቦታዎች ላይ ነው።

እነዚህ ማዕከላት በየክፍለ ከተማውና በየወረዳው ተደራሽነታቸውን እያሰፉ የሚገኙ ሲሆን፣ ማዕከላቱ የሚገኙባቸው አካባቢዎችም እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡-

1ኛ/ አራዳ ክፍለ ከተማ- አራት ኪሎ ፖስታ ቤቱ ጀርባ፤

2ኛ/ ቦሌ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 4 ልዩ ስሙ 24 ቡና ቦርድ፤

3ኛ/ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 1 አሜሪካ ገቢ አዲን የምገባ ማዕከል፤

4ኛ/ ልደታ ክፍለ ከተማ- ልደታ ትምባሆ ሞኖፖል አከባቢ፤

5ኛ/ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 4 ልዩ ቦታው ቄራ መስጊድ ጀርባ 44 ቀበሌ ዋናው መንገድ ላይ፤

6ኛ/ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ- ለቡ መስታወት ፋብሪካ ፊት ለፊት፤

7ኛ/ ልደታ ክፍለ ከተማ- ጌጃ ሰፈር አብደላ ህንጻ ጋር፤

8ኛ/ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ- ቄራ ወደ መብራት ኃይል መውረጃ መንገድ ላይ፤

9ኛ/ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ- ኤግዚቢሽን ጀርባ ሃዲድ ገበያ ጋር፤

10ኛ/ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ- ጨርቆስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ፤

11ኛ/ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 5 ልዩ ቦታው ሳር ቤት ኪንግ ሆቴል ጀርባ፤

12ኛ/ የካ ክፍለ ከተማ- ባልደራስ የቤተመንግስት ጡረተኞች መዝናኛ ክበብ ጀርባ፤

13ኛ/ የካ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 9 ሳሊተ ምህረት ኢኮስኮ ግቢ ውስጥ፤

14ኛ/ የካ ክፍለ ከተማ- ኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጀርባ፤

15ኛ/ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ- አራብሳ ኮንደምኒየም፤

16ኛ/ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 6 አቦ ቤተክርስቲያን ጀርባ፤

17ኛ/ ልደታ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 1 ኳስ ሜዳ፤

18ኛ/ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 8 ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ ፊት ለፊት፤

19ኛ/ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 13 ሲምሲ አደባባይ በላይ፤

20ኛ/ ጉለሌ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 4 ጉለሌ ቀጨኔ መድሃኒአለም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ፤

21ኛ/ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 1 አየር ጤና ቴሌ ጀርባ፤

22ኛ/ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 11 ገላን ጉራ፤

23ኛ/ ጉለሌ ክፍለ ከተማ- ጉለሌ የተቀናጀ ልማት መንደር እንጦጦ፤

24ኛ/ ጉለሌ ክፍለ ከተማ- ሽሮ ሜዳ፤

25ኛ/ የካ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 1 ጉራራ ልማት ተነሺዎች ሰፈር፤

26ኛ/ ቦሌ ክፍለ ከተማ- ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አፓርታማ ሰፈር፤

27ኛ/ ጉለሌ ክፍለ ከተማ- ጉለሌ ምንት ያምር አካባቢ፤

28ኛ/ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ- ለሚ ኩራ ፔፕሲ አካባቢ፤

29ኛ/ ልደታ ክፍለ ከተማ- ልደታ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በጎነት መንደር ይገኛሉ፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review