ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ኢኮ ሁለገብ የህዝብ መዝናኛ ፓርክን መረቁ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ኢኮ ሁለገብ የህዝብ መዝናኛ ፓርክን መረቁ

AMN ግንቦት 13/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ ለከተማች ተጨማሪ የሆነ አዲስ ኢኮ ሁለገብ የህዝብ መዝናኛ ፓርክ መርቀን ለአግልግሎት ክፍት እድርገናል ብለዋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አስኮ አዲስ ሰፈር በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ፥ ለህጻናት፥ ለወጣቶች፥ ለአረጋውያን፥ ድሃ ሃብታም ሳይል አካታች ሕዝብ በጋራ የሚገለገልበት ውብና ማራኪ ሆኖ የተጠናቀቀው ሁለገብ የመዝናኛ ፓርክ ለአካባቢው ነዋሪዎች አማራጭ የመዝናኛ ቦታ ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡

ፓርኩ በውስጡ ፋውንቴይን፥ የእግር ኳስ ሜዳ:፥ የህጻናት መጫወቻ ፥ አምፊ ቲዓትር፥ ዘመናዊ ካፍቴሪያ : ሱቆች: የጁስ ባር፥ ፓርኪንግ፥ ዘመናዊ ሻወር እና መፀዳጃ ቤት እንዲሁም ሰፊ የእግር ጉዞ የሚደረግበት መንገድ ተሟልተውለት በጥራት ተገንብቶለታል ብለዋል፡፡

ቦታው ከዚህ በፊት የቆሻሽ መጣያ የነበረ፥: ህገ ወጦችንም አለ አግባብ ይጠቀመበት የነበረ ሲሆን፥ ዛሬ በርካታ እሴቶች ተጨምረውበት መንፈስን የሚያድስ፥ ህዝብ በጋራ የሚጠቀምበት፥ ንፁህ አካባቢን ፈጥሯል ።

ይህንን ሁለገብ የመዝናኛ ፓርክ ሁላችሁም እየተጠቀማችሁበት እንድትንከባከቡት አደራ እላለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review