AMN- ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
የቅድመ-ምርጫ ሥራዎችና የድምፅ መስጫ ቀንን በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ሃይሉ፣ በመራጮች ምዝገባ ወቅት “ህገ-ወጥ ድርጊቶች እንደተፈፀሙባቸው በተረጋገጡ” ምርጫ ጣቢያዎች ምዝገባው ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ መደረጉን ተናግረዋል።
ምዝገባው በተሰረዘባቸው ምርጫ ጣቢያዎች መራጮች በድምፅ መስጫው እለት እየተመዘገቡ እንዲመርጡ መወሰኑንም አብራርተዋል።

በፀጥታ ችግር ምክንያት በመደበኛው የመራጮች የምዝገባ ጊዜ ምዝገባ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባ እንደተከናወነም ሰብሳቢዋ ተናግረዋል።
የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ አጋማሽ ድረስ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።
በካሳሁን አንዱዓለም