ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒን ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒን ጋር ተወያዩ

AMN-ሐምሌ 6/2018ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ የቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒን ተቀብዬ በወል ጉዳዮች ዙሪያ መክረናል ብለዋል።

‎የሁለትዮሽ ግንኙነታችን መጠናከር እና በጋራ ጥቅሞች ላይ የላቀ ትብብር ለማድረግ በሚያስችሉ እድሎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ለጥልቅ አጋርነት እና ለዘላቂ ወዳጅነት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ እንደምናሳድግ ጽኑ ፍላጎት አለንም ነው ያሉት።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review