AMN ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
ሕዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አደሀ አረፋን በአል ሲያከብር አቅመ ደካሞችን በማስታወስ ሊሆን ይገባል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ1447 ዓ.ሒ የኢድ አል አደሀ አረፋ በአልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫውን የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸህ ሙሀመድ ሸሪፍ፤ የከፍተኛ ምክር ቤቱ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እና ተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዝዳንት ኡስታዝ ሺሐቡዲን ሼህ ኑራ እና ኡስታዝ ጋሊ አባቦር የከፍተኛ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉዳዮች አስተባባሪ ሰጥተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸህ ሙሀመድ ሸሪፍ፤ ህዝበ ሙስሊም የመረዳዳት ልምዱን በመጠቀም አቅመ ደካሞችን እና ምስኪኖችን ማስታወስ ይገባዋል ብለዋል፡፡

ከበአሉ ጥቂት ቀናት በኋላ በሚካሄደዉ የ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ላይ ህዝቡ ሊሳተፍ እንደሚገባም አደራ ብለዋል።
የበአሉ ዋነኛ መገለጫ የሆነው የስግደት ስነስርዓት በዋነኝነት በአዲስ አበባ እስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን በተጨማሪም በክፍለ ከተማ ደረጃ በተዘጋጁ የመስገጃ ስፍራዎች እንደሚሆን ተገልጿል፡፡