ከንቲባ አዳነች አቤቤ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በጽዳት ንቅናቄ አስጀመሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በጽዳት ንቅናቄ አስጀመሩ

AMN – ሰኔ 13/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በጽዳት ንቅናቄ አስጀምረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ፤ ዛሬ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በጽዳት ንቅናቄ አስጀምረናል ብለዋል፡፡

የአንድ ከተማ ዓለም አቀፍ መለኪያው ፅዳት፣ ውበት፣ አረንጓዴነት ነው ለዚህም ነው ውብ ፅዱ አረንጓዴ ከተማን ለመፍጠር ህዝባችንን አሳትፈን ባለድርሻ አካላትን በማነቃነቅ ውጤታማ ስራ ሰርተን በአፍሪካ ከ10 ፅዱ ከተሞች እንዷ ለመሆን የቻልነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባ ከዚህ በፊት የምትወቀስበት ፅዱ፣ ውብ አለመሆንዋን እና የአረንጓዴ ከተማ ሽፋንዋ እየቀነሰ በመሄዱ በሰራናቸው ተከታታይ ስራዎች መቀልበስ ችለናል ብለዋል፡፡

ፅዳት የዘወትር ስራ ነው፣ ፅዳት ባህል መሆን መቻል አለበት ያሉት ከንቲባዋ ፤ ሁልጊዜ ከህይወታችን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን የተሳሰረ መሆኑን በሁሉም ኣካባቢ ማረጋገጥ ይኖርብል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ፅዳት ከቤት ይጀምራል በመሆኑም ሁላችንም በየአካባቢያችንና በየተቋማችን ባህል አድረገን መያዝ ይገባልም ነው ያሉት።

ይህ ባህል እስኪሆን ያለእረፍት፣ በትጋት መስራት ሁሌም ክትትል በማድረግ የፅዳት አምባሳደር እንድንሆን አደራ ማለት እፈልጋለሁ ሲሉም ከንቲባዋ መልእክት አስተላልፈዋል፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review