በምርጫው የሴቶች ሁለንተናዊ ጥቃት እንዳይፈጠር መሰራቱ ለምርጫው ስኬታማነትን ፈጥሯል- የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር

AMN- ሰኔ 14/2018 ዓ.ም

በምርጫው የሴቶች ሁለንተናዊ ጥቃት እንዳይፈጠር መሰራቱ ለምርጫው ስኬታማነትን ፈጥሯል ሲሉ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሕብረት አባሆይ ተናገሩ።

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ማሳወቂያ መርኀ-ግብር በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ በምርጫው ሴቶች የነበራቸውን ተሳትፎና ሴቶች ከማንኛውም ጥቃት ነፃ ሆነው እንዲመርጡ የተደረገበትን መንገድ ያቀረቡት የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሕብረት አባሆይ፣ የሴቶች ሁለንተናዊ መብት በምርጫው ተጠብቋል ብለዋል።

በምርጫው ሴቶች ከየትኛውም ጊዜ በላይ የነበራቸው ተሳትፎ ታሪካዊና ወደፊትም መቀጠል ያለበት መሆኑን ገልጸዋል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review