AMN-ሰኔ 17/2018 ዓ.ም

ኮሎምቢያ ዲ.ሪ ኮንጎን 1ለ0 በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን መቀላቀል ቻለች።
ብቸኛውን ግብ የክሪስታል ፓላሱ ተከላካይ ዳንኤል ሙኖዝ አስቆጥሯል።

በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኡዝቤኪስታንን ያሸነፈችው ኮሎምቢያ ምድብ 11ን በስድስት ነጥብ እየመራች ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች።
ኮሎምቢያ የምድቡ የበላይነቷን ለማስጠበቅ በቀጣይ አራት ነጥብ ካላት ፖርቹጋል ጋር ትጫወታለች።

ከፖርቹጋል ጋር አቻ በመለያየት የጀመረችው ዲ.ሪ ኮንጎ በውድድሩ ለመቆየት በቀጣይ ኡዝቤኪስታንን ትገጥማለች።
በሌላ ጨዋታ በምድብ 12 ክሮሺያ አንቴ ቡድሚር ባስቆጠረው ግብ ፓናማን 1ለ0 አሸንፋለች።

በቀጣይ እንግሊዝን የምትገጥመው ፓናማ ከውድድሩ ውጪ ስትሆን ፣ ሦስት ነጥብ ያላት ክሮሺያ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ጋናን ትገጥማለች።
በሸዋንግዛው ግርማ