AMN ሰኔ 30 / 2018 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ከሚገኙት የሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ዶ/ር ጌዲዎን የኢትዮጵያ እና ሩስያ ወዳጅነት ዘመናትን የተሻገር መሆኑን ገልጸዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች በወቅታዊ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

ሚኒስትሮቹ ከፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ ግንኙነት ባሻገር የኢትዮጵያ እና ሩስያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በንግድ፣ኢንቨስትመንት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ ያለው ትብብር የበለጠ በሚጠናከርበት መንገድ ዙሪያም መክረዋል።

ብሪክስን ጨምሮ በሌሎች የባለብዙ ወገን የግንኙነት የዲፕሎማሲ መድረኮች ትብብራቸውን ማጠናከር እንደሚገባ በመወያየታቸዉን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡