AMN-ሐምሌ 6/2018ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥ ጀምሯል፡፡
የከተማ አስተዳደሩን የኦዲት አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ እያቀረቡ የሚገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ መቻሉ ናቸው፡፡

ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ውሎው የምክር ቤቱ ስትራቴጂክ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያደመጠ ሲሆን፣ አሁን በዋና ኦዲተሩ እየቀረበ ባለው ሪፖርት ላይም የምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡
በትዝታ መንግሥቱ