AMN- ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የቀድሞው የኳታር አሚር እና የሀገር አባት ሼክ ሐማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘንና ክብራቸውን ለመግለጽ ወደ ኳታር መዲና ዶሃ ገብተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋዊ የሐዘን ጉብኝት በኢትዮጵያና በኳታር መካከል ያለውን የረጅም ዘመን ወዳጅነትና ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ የሚያንጸባርቅ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ጉብኝቱ፣ የቀድሞው አሚር በቀጣናውና በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ጥለውት የሄዱትን ታላቅ መሪነትና የማይረሳ አሻራ ክብር የሚሰጥ መሆኑ ተመልክቷል።
የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ባወጣው መረጃ ፣ የሼክ ሐማድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ነፍስ በሰላም እንድታርፍ በመመኘት፣ ለኳታር መሪዎች፣ ለንጉሣዊው ቤተሰብ እና ለመላው የኳታር ሕዝብ በዚህ አስቸጋሪ የሐዘን ወቅት መጽናናትንና ብርታትን ተመኝቷል።