ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኳታሩ አሚር አቀባበል ተደረገላቸው

AMN – ሐምሌ 06/2018 ዓ.ም.

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በኳታር መንግሥት አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሐመድ አል ታኒ፣በሉሳይል ንጉሣዊ ቤተ መንግሥት ልዩ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበል ስነስርዐቱ ላይ የኳታር ንጉሳዊ ቤተሰብ አባላት፣ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ ሙሐመድ ቢን አብዱልራህማን ቢን ጃሲም አል ታኒ፣ እንዲሁም በቅርቡ ህይወታቸው ያለፈው የቀድሞ የሃገሪቱ አሚር ልጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያን መንግሥትና ህዝብ በመወከል በቀድሞው የኳታር አሚር ሼክ ሐመድ ቢን ኸሊፋ አል ታኒ ህልፈትን አስመልክቶ ሀዘናቸውን ለመግለጽ ዛሬ ምሽት ወደ ኳታር ማቅናታቸው ይታወሳል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ በኢትዮጵያና በኳታር መካከል ያለውን ጠንካራና የረጅም ጊዜ ወዳጅነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ገልጿል።

በሉሳይል ንጉሣዊ ቤተ መንግሥት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ልዩ አቀባበል መደረጉንም የኳታር መንግሥት አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review