AMN – ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አመራሮች እና ሠራተኞች ለ2ኛ ጊዜ ያከናወኑት የስፖርት ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።
በዚህም መሰረት በእግር ኳስ የፍጻሜ ጨዋታ የቴሌቪዥን ዘርፍ የኢንጅነሪንግ ዘርፍን በመለያ ምት በመርታት የዋንጫው ባለቤት መሆን ችሏል።
በዕለቱ ከቴሌቪዥን እና የኢንጅነሪንግ ዘርፍ ፍጻሜ ጨዋታ በተጨማሪ፣ የአመራሮች የእግር ኳስ ውድድርም የተካሄደ ሲሆን፤ በሩጫ፣ በሜዳ ቴኒስ እና በገመድ ጉተታ ተመልካቾችን ያዝናኑ የተለያዩ ውድድሮችም ተከናውነዋል።

በውድድሮቹ አሸናፊ ለሆኑ ቡድኖችና ተወዳዳሪዎች ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ዲባባ እና ከሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እጅ የተዘጋጀላቸው ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በሸዋንግዛው ግርማ