AMN- ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም

ማንችስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ በኢትሃድ ስታዲየም ቦርንማውዝን አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማርከስ ታቨርኒኤር ቦርንማውዝን ቀዳሚ ማድረግ ችሎ የነበረ ቢሆንም፣ ሲቲ በማርክ ገሂ እና በዮሽኮ ግቫርዲዮል ግቦች አሸንፎ መውጣት ተችሏል።
ፔፕ ጋርዲዮላን የተካው ኤንዞ ማሬስካ የውድድር ዓመቱን በድል ጀምሯል። አንዶኒ ኢራዮላን የተካው ማርኮ ሮሰ ቦርንማውዝን ባለድል ማድረግ ሳይችል ቀርቷል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተከናወነ ሌላ ጨዋታ አስቶን ቪላ በብራይተን 4 ለ 0 በሰፊ ውጤት ተሸንፏል።
ለብራይተን ጃክ ሂንሽልውድ ሁለት ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፤ የማክሲም ዲ ካይፐር አንድ ግብ እና ቪክቶር ሊንደሎፍ በራሱ ላይ ያስቆጠራት ግብ ለብራይተን ሰፊ ድል አስገኝተዋል።

በአስቶን ቪላ በኩል አማካዩ ጆአኦ ጎሜስ በ40ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ መወገዱ ለቡድኑ ፈተና ሆኖ ነበር።
በሸዋንግዛው ግርማ