ኢትዮጵያ አሸነፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ የላትም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

You are currently viewing ኢትዮጵያ አሸነፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ  የላትም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

AMN- መስከረም 25/2019 ዓ.ም

ኢትዮጵያ አሸነፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ የላትም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የኢፌዴሪ 7ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)ን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ በድጋሚ ሾሟል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃለ መሃላ ከመፈጸሙ በኋላ እያደረጉት ባለው ንግግር ኢትዮጵያውያን ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በበዙ ፈተናዎች አልፎ መሳካቱን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤት ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት ፣ 54 ሚሊዮን ዜጎች በብዙ ውዥንብሮች፣ ዛቻዎችና ተግዳሮቶች መካከል አልፈው ድምጻቸውን በመስጠት ለዲሞክራሲ ስርዓት መጎልበት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ የዲሞክራሲ ባህልም በምርጫ ወቅት ይፈተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሂደቱ የሀገሪቱን የዲሞክራሲ መሰረት ያጠናከረና በታሪክ የሚዘከር መሆኑን ተናግረዋል።

በምርጫው አሸናፊ ና ተሸናፊ ፓርቲ ሊኖር ይችላል ፣ ኢትዮጵያ አሸነፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራት ግን አረጋግጥላችኋለሁ ብለዋል፡፡

የሀገር ግንባታ የአንድ ወገን ብቻ ጥረት አለመሆኑን በማስረገጥ ቤት በአንድ እጅ እንደማይገነባ ሁሉ ሀገርም የምትጸናው ዜጎች እንደ ወንድማማች እኩል ተያይዘው ሲራመዱ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review