አቶ ሙሉቀን ታሪኩ ከቀድሞ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረ እግዚኣብሔር የስራ ርክክብ አደረጉ

AMN- መስከረም 26/2019 ዓ.ም

አዲስ የተሾሙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታሪኩ ከቀድሞው የቢሮው ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረ እግዚኣብሔር የስራ ርክክብ አደረጉ።

አቶ ሃፍታይ ገብረ እግዚኣብሔር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ሁለቱ የስራ ሃላፊዎች መልካም የስራ ዘመን ምኞቶቻቸውን ተለዋውጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ማሕበረሰብ ለሁለቱም ተሿሚዎች የተሳካ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review