AMN – ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም
በታሪካዊ ጠላቶች የተፈጠሩ ኃይሎች በመከላከያ ሠራዊት ተሸንፈው መበታተናቸውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) ገለጹ።
ዶክትር አረጋዊ በርሔ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በታሪካዊ ጠላቶች “ጽምዶ” በሚል ስብስብ የተፈጠሩት ኃይሎች፣ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ድል ተመተው መበታተናቸውን ተናግረዋል።
መከላከያ ሠራዊት ከጥንት እስከ አሁን ኢትዮጵያን ከመጠበቅ እና ሉዓላዊነቷን ከማስጠበቅ አንፃር ጉልህ ሚና ማበርከቱን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ በጥንት ጊዜም ታሪካዊ ጠላቶች ወረራ ለመፈጸም ሞክረው በኢትዮጵያ ሠራዊት ተሸንፈው መመለሳቸውን አስታውሰዋል።
በቅርብ ጊዜም በታሪካዊ ጠላቶች “ጽምዶ” የተሰኘ ስብስብ እንደተፈጠረ በመግለጽ፣ እነዚህ ኃይሎች ተሰባስበው ሀገርን ለማተራመስ ሙከራ አድርገው እንደነበር ጠቅሰዋል።

በዚህ እኛ ምስክር በሆንንበት ወቅት “ጽምዶ” የተሰኘው ስብስብ በመከላከያ ሠራዊት ድል ተሸንፎ መበታተኑን ገልጸው፣ በዚህም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሁሌም የአሸናፊነትና የድል ባለቤት መሆኑን አረጋግጠዋል።
የመከላከያ ሠራዊት በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱን በሚመጥን መልኩ በብቃት የተደራጀ መሆኑም ተመላክቷል።
በየሻምበል ምህረት