አዲስ አበባ የ2026 የዓለም እና የአፍሪካ ዳማ ፌስቲቫልን ልታስተናግድ ነው

You are currently viewing አዲስ አበባ የ2026 የዓለም እና የአፍሪካ ዳማ ፌስቲቫልን ልታስተናግድ ነው

AMN-ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ የ2026 እ.ኤ.አ የዓለም እና የአፍሪካየዳማ ፌስቲቫልን የማስተናገድ እድል አግኝታለች።

በውድድሩ ዙሪያም ዛሬ በወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል። የወጣቶችና ስፖርት ሚንስቴር ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለፀው ከ40 ሀገራት የተውጣጡ 80 ስፖርተኞች ይሳተፋሉ።

በመግለጫው ላይ የተገኙት በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ አበባ አማረ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ አሁን እየሰራች ካለው ሰፊ ስራ መነሻ ውድድሩን ማዘጋጀት ይገባታል ብለዋል።

ፌስቲቫሉ በሀገራችን ያለውን የዳማ ስፖርት ከማነቃቃት ባለፈ ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም ሀብት ለእንግዶች ለማሳየት ጥሩ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ የሚከናወነው የአፍሪካ እና የዓለም የዳማ ውድድር በአይነትም በይዘትም የመጀመሪያው መሆኑን የአፍሪካ ዳማ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ኦማር ታየር ገልፀዋል። ውድድሩ በሰባት ካታጎሪዎች እንደሚከናወን ሃላፊው ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ዳማ አሶሴሽን ፕሬዘዳንት ታድሎ ደሳለኝ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ጥሩ ተፎካካሪ እንድትሆን ወራትን ወስደው ተወዳዳሪ መመልመላቸውን ተናግረዋል።

ከመላ ኢትዮጵያ ጥሩ ስፖርተኞችን ለማግኘት እንደጣሩ የተናገሩት ሃላፊው ውድደሩን ከማዘጋጀት ባለፈ ጥሩ ውጤት ለማምጣት ተዘጋጅተናል ብለዋል።

ውድድሩ ከህዳር 24 እስከ ታኅሣሥ 06/2019 ዓ/ም በአዲስ አበባ ግራንድ ኤሊያና ሆቴል እና የአድዋ ድል መታሰቢያ እንደሚካሄድ በመግለጫው ተነስቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review