ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመጀመሪያዎቹን 26 ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተለወጡ አውቶብሶች ሥራ አስጀመሩ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመጀመሪያዎቹን 26 ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተለወጡ አውቶብሶች ሥራ አስጀመሩ

AMN- ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመጀመሪያዎቹን 26 ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የተለወጡ አውቶብሶች ሥራ አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዛሬ የመጀመሪያዎቹ 26 የከተማ አውቶብሶች ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ተለውጠው ሥራ ላይ በመዋላቸው የተሰማኝን ደስታ መግለጽ እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት ወራት የተፈጥሮ ጋዝ ምርትን ከሚመረትበት ስፍራ ወደ አዲስ አበባ የማጓጓዝ፣ የጋዝ ማደያዎችን የማዘጋጀት እና የከተማ አውቶብሶችን ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የመለወጥ ሰፊ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል ብለዋል።

ይህ ታሪካዊ እርምጃ በነዳጅ ግዢ ላይ የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያስቀርም አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም የሕዝብ ትራንስፖርት የሥራ ማስኬጃ ወጪን በመቀነስ የዜጎችን የጉዞ ታሪፍ በግማሽ ያቃልላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በራስ አቅም ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የመለወጡ ተግባር ደግሞ የሀገር ውስጥ አቅምንና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል።

በቀጣይም በነዳጅ ላይ ያለንን ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት እና ሀገር ውስጥ እያመረትን ያለነውን የተፈጥሮ ጋዝ በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችሉ 400 አዳዲስ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ አውቶብሶች በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባሉም ነው ያሉት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አክለውም፤ በምግብ፣ በቤት እና በትራንስፖርት ዘርፎች ላይ ተጨባጭ ሥራዎችን በማከናወን በዜጎች ሕይወት ላይ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የተጀመሩት አበረታች ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review