ቃል ርዕይን ይገልጣል፤ ተግባር ደግሞ ርዕይን ወደ እውነታ ይለውጣል – ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

You are currently viewing ቃል ርዕይን ይገልጣል፤ ተግባር ደግሞ ርዕይን ወደ እውነታ ይለውጣል – ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

AMN- ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም

የመሪዎችን ንግግሮች፣ መልዕክቶችና ታሪካዊ ክንውኖች መዝግቦ ማቆየት የሀገርን የለውጥ ጉዞና ታሪክን ለትውልድ ለማስተላለፍ ወሳኝ መንገድ ነው።

‎በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በየዓመቱ እየተዘጋጀ ለአንባቢያንና ለትውልድ የሚታተመው «ከመስከረም እስከ መስከረም» ተከታታይ መጽሐፍ፤ ዘጠነኛውን ምዕራፍ ይዞ ቀርቧል።

ይህ ዕትም ከቃል ወደ ተግባር፣ ከተስፋ ወደ ተጨበጠ ሐብት የተሸጋገረውን የአፈጻጸምና የእመርታ ጉዞን ያስቃኛል።

በዚህም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመስከረም 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 2019 ዓ.ም በተለያዩ ክንውኖችና ክብረ በዓላት ላይ ያደረጓቸው ንግግሮች እና ያስተላለፏቸውን መልዕክቶች ይዟል።

በውስጡም የሀገራዊ ለውጥ፣ ልማት፣ የኢኮኖሚ እመርታ፣ የብሔራዊ ክብርና የዓለም አቀፍ ትብብርን ከቀጣይ ርዕይ ጋር ያስተሳሰሩ መልዕክቶች ተሰንደዋል።

‎ከቃል እስከ ክንውን፣ ከርዕይ እስከ ውጤት፤ የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ ለታሪክ ሰንዶ የሚያስቀምጥ የአመራር፣ የአፈጻጸምና የሀገር ግንባታ ተጨባጭ ምስክር።

‎ከቃል ባሻገር፣ በተግባር የተረጋገጠ እመርታ፤ መልካም ንባብ!

‎ሙሉ መጽሐፉን ለማንበብ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ ↓

‎https://pmo.gov.et/…/efb1bd26-fc75-4c5a-96d1…

‎#PMOEthiopia

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review