የወንዝ ዳርቻ ልማቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው

You are currently viewing የወንዝ ዳርቻ ልማቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው

AMN- ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እየተተገበሩ ያሉ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ከተማዋን ያማረ ገፅታ ከማላበስ ባሻገር የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ እና ስፖርታዊ ባህልን በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ተገለፀ።

አዲስ ተመርቆ ወደ ሥራ በገባው ከቀጨኔ መድሃኒያለም እስከ ጨፌ ሜዳ ባለው የወንዝ ዳርቻ ልማት የግር ጉዞን ጨምሮ የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የማህበረሰብ ስፖርት ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ መሰረተ ልማቶች በተለይም የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ረዘም ያሉ የእግር ጉዞዎችን ለማድረግ እና የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ለማድረግ ምቹ ሁኔታ እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ መሰረተ ልማቶች ስፖርትን ባህል በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው ያሉት አቶ እንግዳወርቅ፤ በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ልማድ እየዳበረ መምጣቱን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ከቀጨኔ መድሃኒያለም እስከ ጨፌ ሜዳ በተዘረጋው የወንዝ ዳርቻ ልማት የግር ጉዞ ሲያደርጉ ያገኘናቸው የራስ ሀይሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማእከል አባላት እና ዋና አሰልጣኛቸው ማስተር አሳምነው ዘበነ ፤ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለማቋረጥ ማድረግ ጤና ለማስጠበቅ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል፡፡

በመሰረተ ልማቶቹ የተገኘውን ዕድል በአግባቡ እየተጠቀሙበት እንደሚገኙም አብራርተዋል።

በሙሳ አሕመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review