የተቀየረው የአዲስ አበባ የኮሪደርና ወንዞች ዳርቻዎች ታሪክ

You are currently viewing የተቀየረው የአዲስ አበባ የኮሪደርና ወንዞች ዳርቻዎች ታሪክ

AMN – ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ እና የኮሪደር ልማቶች አዋቂዎች የሚዝናኑባቸው፣ ህፃናት የሚጫወቱባቸው፣ ጤናቸውን የሚጠብቁባቸውና ከዕለት ተዕለት የሥራ ድካም እፎይታ የሚያገኙበት ምቹ ስፍራዎች ሆነዋል።

ይህንን የከተማ ኑሮ ውበትና ትርጉም በተግባር እያሳየች ያለችው አዲስ አበባ፤ የወንዞቿ ዳርቻና የኮሪደር ልማቶቿ ከቀድሞው ገጽታቸው ተላቀው ለመዝናኛ፣ ለእረፍት፣ ለእግር ጉዞና ለማህበራዊ ትስስር ምቹ ወደሆኑ የሕዝብ መገናኛ ስፍራዎች እየተቀየሩ ይገኛሉ።

በተለይም በኮሪደርና በወንዞች ዳርቻ ልማቶች ላይ የተገነቡት ዘመናዊ የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎች ለልጆች ደስታን፣ ለወላጆች እፎይታን፣ ለቤተሰቦች ደግሞ በጋራ የሚያሳልፉበትን ምቹ ሁኔታ እየፈጠሩ ነው።

ይህም አደስ አበባ ለሕፃናት እድገትና ደስታ ቅድሚያ የምትሰጥ፣ ለቀጣዩ ትውልድ ምቹ አካባቢ የምትፈጥር ከተማ የመሆን ጉዞዋን ያመላክታል።

በተመሳሳይ የተስፋፉትና የዘመኑት የስፖርት መሠረተ ልማቶች፣ የከተማዋን የቱሪዝም መስህብነት ከማሳደግ ባለፈ፣ ለአካል ብቃትና ለጤናማ ኑሮ ማዕከል እየሆኑ ነው።

የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የውጭ ዲፕሎማቶች እነዚህን ስፍራዎች ለመዝናኛና ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየተጠቀሙባቸው መሆናቸውም፣ የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተመራጭነት የሚያጎላ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ የአካታች መሠረተ ልማት ግንባታ፣ የፓርኮች ውበትና ምቾት፣ እንዲሁም የተሟላ አገልግሎት መስፋፋት ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች በእኩልነት የሚጠቀሙባቸውን የጋራ ሀብቶች እየፈጠረ ነው።

እነዚህ ስፍራዎች የከተዋ የውበት መገለጫዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ የማህበራዊ ትስስር፣ የጤናማ አኗኗርና የሰው ልጅ ደስታ መሠረቶችም ናቸው።

የከተማ ልማት ትልቁ ዓላማ መሠረተ ልማትን መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎች በተገነቡት መሠረተ ልማቶች ውስጥ የተሻለ ሕይወት እንዲኖሩ ማስቻል ነው።

ስለዚህ እነዚህ የመዝናኛና የእረፍት ስፍራዎች በዕለት ተዕለት ሥራ የደከመውን አዕምሮ ለማደስ፣ ከቤተሰብና ከወዳጆች ጋር ደስታ የተሞላበት ጊዜን ለማሳለፍ፣ ለአካል ብቃትና ለጤናማ ኑሮ እንዲጠቀምባቸው ሁሉንም ይጋብዛሉ።

አዲስ አበባ የሚሠሩባት፣ የሚኖሩባት፣ የሚዝናኑባት፣ ጤናን የሚጠብቁባት የቱሪዝም ማዕከል እየሆነች መምጣቷን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review