የብልፅግና ፓርቲ የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ

You are currently viewing የብልፅግና ፓርቲ የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ

AMN- ጥቅምት 29/2019 ዓ.ም

የብልፅግና ፓርቲ የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤትና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በግምገማው የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የፓርቲ የሥራ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በብልፅግና ፓርቲ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱም በሩብ ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ የሥራ አቅጣጫዎች በጥልቀት ተገምግመዋል።

በመድረኩ የሥራ አፈጻጸሙ ጠንካራ ጎኖች እና ደካማ ጎኖች ተለይተውም መገምገማቸውን ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም የተገኙ ልምዶችን ማጠናከር፣ የአፈጻጸም ክፍተቶችን ማረም እና ቀጣይ ሥራዎችን በተሻለ ውጤታማነት ለመፈጸም በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት ተደርጓል።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በመድረኩ፤ የቀጣይ የሥራ አፈጻጸምን ለማጠናከር ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review